ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 19:2-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. ቀን ለሌላው ቀን ይናገራል፤ሌሊትም ለሌሊት ዕውቀትን ይገልጣል፤

3. ንግግር የለም፤ ቃል የለም፤ድምፃቸው በጆሮ የሚሰማ አይደለም።

4. ያም ሆኖ ድምፃቸው ወደ ምድር ሁሉ፣ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ይወጣል።እርሱ በሰማያት ለፀሓይ ድንኳን ተክሎአል፤

5. ፀሓይም ከእልፍኙ እንደሚወጣ ሙሽራ ይወጣል፤ወደ ግቡም እንደሚሮጥ ብርቱ ሰው ደስ ይለዋል።

6. መውጫው ከሰማያት ዳርቻ ነው፤ዑደቱም እስከ ሌላኛው ዳርቻ ነው፤ከትኩሳቱም የሚሰወር የለም።

7. የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው፤ነፍስንም መልሶ ያለመልማል፤ የእግዚአብሔር ሥርዐት የታመነ ነው፤አላዋቂውን ጥበበኛ ያደርጋል።

8. የእግዚአብሔር ሕግጋት ትክክል ናቸው፤ልብን ደስ ያሰኛሉ። የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው፤ዐይንን ያበራል።

9. እግዚአብሔርን መፍራት ንጹሕ ነው፤ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል። የእግዚአብሔር ፍርድ የታመነ፣ሁለንተናውም ጻድቅ ነው፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 19