ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 22:17-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. ዐጥንቶቼን ሁሉ አንድ በአንድ መቍጠር እችላለሁ፤እነርሱም አፍጥጠው ይመለከቱኛል።

18. ልብሶቼን ተከፋፈሉ፤በእጀ ጠባቤም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ።

19. አንተ ግን፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ ከእኔ አትራቅ፤አጋዤ ሆይ፤ እኔን ለመርዳት ፍጠን።

20. ነፍሴን ከሰይፍ ታደጋት፤ውድ ሕይወቴንም ከውሾች ጡጫ አድናት።

21. ከአንበሶች አፍ አድነኝ፤ከአውራሪስ ቀንድም ታደገኝ።

22. ስምህን ለወንድሞቼ እነግራለሁ፤በጉባኤም መካከል አመሰግንሃለሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 22