ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 22:26-31 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

26. ምስኪኖች በልተው ይጠግባሉ፤ እግዚአብሔርን የሚሹትም ያመሰግኑታል፤ልባችሁም ለዘላለም ሕያው ይሁን!

27. የምድር ዳርቻዎች ሁሉ ያስታውሳሉ፤ወደ እግዚአብሔርም ይመለሳሉ፤የሕዝቦች ነገዶች ሁሉ፣በፊቱ ይሰግዳሉ።

28. መንግሥት የእግዚአብሔር ናትና፤ሕዝቦችንም የሚገዛ እርሱ ነው።

29. የምድር ከበርቴዎች ይበላሉ፤ይሰግዱለታልም፤ነፍሱን በሕይወት ማቆየት የማይችለው፣ ወደ ዐፈር፣ተመላሽ የሆነው ሁሉ በፊቱ ይንበረከካል።

30. የኋለኛው ትውልድ ያገለግለዋል፤ለመጪው ትውልድ ስለ ጌታ ይነገረዋል።

31. ገና ላልተወለደ ሕዝብ፣ጽድቁን ይነግራሉ፤እርሱ ይህን አድርጎአልና።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 22