ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 23:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፤አንዳች አይጐድልብኝም።

2. በለመለመ መስክ ያሳርፈኛል፤በዕረፍት ውሃ ዘንድ ይመራኛል፤

3. ነፍሴንም ይመልሳታል።ስለ ስሙም፣በጽድቅ መንገድ ይመራኛል።

4. በሞት ጥላ ሸለቆ ውስጥ፤ብሄድ እንኳ፣አንተ ከእኔ ጋር ስለ ሆንህ፣ክፉን አልፈራም፤በትርህና ምርኵዝህ፣እነርሱ ያጽናኑኛል።

5. ጠላቶቼ እያዩ፣በፊቴ ማዕድ አዘጋጀህልኝ፤ራሴን በዘይት ቀባህ፤ጽዋዬም ሞልቶ ይፈስሳል።

6. በሕይወቴ ዘመን ሁሉ፣በጎነትና ምሕረት በእርግጥ ይከተሉኛል፤እኔም በእግዚአብሔር ቤት፣ለዘላለም እኖራለሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 23