ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 25:10-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. ኪዳኑንና ሥርዐቱን ለሚጠብቁ፣ የእግዚአብሔር መንገድ ሁሉ ቸርነትና እውነት ናቸው።

11. እግዚአብሔር ሆይ፤ ኀጢአቴ ታላቅ ነውና፣ስለ ስምህ ይቅር በልልኝ።

12. እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ማን ነው?በተመረጠለት መንገድ ያስተምረዋል።

13. ዘመኑን በተድላ ደስታ ያሳልፋል፤ዘሩም ምድርን ይወርሳል።

14. እግዚአብሔር ምስጢሩን ከሚፈሩት ወዳጆቹ አይሰውርም፤ኪዳኑንም ይገልጥላቸዋል።

15. ዐይኖቼ ሁል ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ናቸው፤እግሮቼን ከወጥመድ የሚያላቅቃቸው እርሱ ነውና።

16. እኔ ብቸኛና የተጨነቅሁ እንደ መሆኔ፣ወደ እኔ ተመለስ፤ ምሕረትም አድርግልኝ።

17. የልቤ መከራ በዝቶአል፤ከጭንቀቴ ገላግለኝ።

18. ጭንቀቴንና መከራዬን ተመልከት፤ኀጢአቴንም ሁሉ ይቅር በለኝ።

19. ጠላቶቼ እንዴት እንደ በዙ ተመልከት፤እንዴት አምርረው እንደሚጠሉኝ እይ።

20. ነፍሴን ጠብቃት፤ ታደገኝም፤መጠጊያዬ ነህና አታሳፍረኝ።

21. አንተን ተስፋ አድርጌአለሁና፣ታማኝነትና ቅንነት ይጠብቁኝ።

22. አምላክ ሆይ፤ እስራኤልን፣ከመከራው ሁሉ አድነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 25