ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 28:1-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ እጣራለሁ፤ዐለቴ ሆይ፤ ሰምተህ እንዳልሰማ አትሁንብኝ፤አንተ ዝም ካልኸኝ፤ወደ ጒድጓድ እንደሚወርዱ እሆናለሁ።

2. ለርዳታ በጮኽሁ ጊዜ፣ወደ ቅዱስ ማደሪያህ፣እጆቼን በዘረጋሁ ጊዜ፣የልመናዬን ቃል ስማ።

3. በልባቸው ተንኰል እያለ፣ከባልንጀሮቻቸው ጋር በሰላም ከሚናገሩ፣ከክፉ አድራጊዎችና፣ከዐመፃ ሰዎች ጋር ጐትተህ አትውሰደኝ።

4. እንደ ሥራቸው፣እንደ ክፉ ተግባራቸው ክፈላቸው፤እንደ እጃቸው ሥራ ስጣቸው፤አጸፋውን መልስላቸው።

5. ለእግዚአብሔር ሥራ ግድ ስለሌላቸው፣ለእጆቹም ተግባራት ስፍራ ስላልሰጡ፣እርሱ ያፈርሳቸዋል፤መልሶም አይገነባቸውም።

6. የልመናዬን ቃል ሰምቶአልና፣ እግዚአብሔር የተባረከ ይሁን።

7. እግዚአብሔር ብርታቴና ጋሻዬ ነው፤ልቤ በእርሱ ይታመናል፤ እርሱም ዐግዞኛል፤ልቤ ሐሤት አደረገ፤በዝማሬም አመሰግነዋለሁ።

8. እግዚአብሔር ለሕዝቡ ብርታታቸው ነው፤ለቀባውም የመዳን ዐምባ ነው።

9. ሕዝብህን አድን፤ ርስትህንም ባርክ፤እረኛ ሁናቸው፤ ለዘላለሙም ዐቅፈህ ያዛቸው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 28