ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 28:3-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. በልባቸው ተንኰል እያለ፣ከባልንጀሮቻቸው ጋር በሰላም ከሚናገሩ፣ከክፉ አድራጊዎችና፣ከዐመፃ ሰዎች ጋር ጐትተህ አትውሰደኝ።

4. እንደ ሥራቸው፣እንደ ክፉ ተግባራቸው ክፈላቸው፤እንደ እጃቸው ሥራ ስጣቸው፤አጸፋውን መልስላቸው።

5. ለእግዚአብሔር ሥራ ግድ ስለሌላቸው፣ለእጆቹም ተግባራት ስፍራ ስላልሰጡ፣እርሱ ያፈርሳቸዋል፤መልሶም አይገነባቸውም።

6. የልመናዬን ቃል ሰምቶአልና፣ እግዚአብሔር የተባረከ ይሁን።

7. እግዚአብሔር ብርታቴና ጋሻዬ ነው፤ልቤ በእርሱ ይታመናል፤ እርሱም ዐግዞኛል፤ልቤ ሐሤት አደረገ፤በዝማሬም አመሰግነዋለሁ።

8. እግዚአብሔር ለሕዝቡ ብርታታቸው ነው፤ለቀባውም የመዳን ዐምባ ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 28