ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 33:18-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

18. እነሆ፤ የእግዚአብሔር ዐይኖች በሚፈሩት ላይ ናቸው፤ምሕረቱንም በሚጠባበቁት ላይ አትኵረዋል።

19. በዚህም ነፍሳቸውን ከሞት ያድናል፤በራብ ዘመንም በሕይወት ያኖራቸዋል።

20. ነፍሳችን እግዚአብሔርን ተስፋ ታደርጋለች፤እርሱ ረዳታችንና መጠጊያችን ነው።

21. ልባችን በእርሱ ደስ ይለዋል፤በቅዱስ ስሙ ታምነናልና።

22. እግዚአብሔር ሆይ፤ ተስፋ ባደረግንህ፣በእኛ ላይ ምሕረትህ ትሁን።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 33