ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 34:1-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔርን ሁል ጊዜ እባርከዋለሁ፤ምስጋናውም ዘወትር ከአፌ አይለይም።

2. ነፍሴ በእግዚአብሔር ተመካች፤ትሑታንም ይህን ሰምተው ሐሤት ያደርጋሉ።

3. ኑና ከእኔ ጋር እግዚአብሔርን አክብሩት፤ስሙንም በአንድነት ከፍ ከፍ እናድርግ።

4. እግዚአብሔርን ፈለግሁት፤ እርሱም መለሰልኝ፤ከፍርሀቴም ሁሉ አዳነኝ።

5. ወደ እርሱ የሚመለከቱ ያበራሉ፤ፊታቸውም ከቶ አያፍርም።

6. ይህ ችግረኛ ጮኸ፤ እግዚአብሔርም ሰማው፤ከመከራውም ሁሉ አዳነው።

7. እግዚአብሔርን በሚፈሩት ዙሪያ የእግዚአብሔር መልአክ ይሰፍራል፤ያድናቸዋልም።

8. እግዚአብሔር ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እዩ፤እርሱን መጠጊያ የሚያደርግ ምንኛ ቡሩክ ነው!

9. እናንተ ቅዱሳኑ፤ እግዚአብሔርን ፍሩት፤እርሱን የሚፈሩት አንዳች አያጡምና።

10. አንበሶች ሊያጡ፣ ሊራቡም ይችላሉ፤ እግዚአብሔርን የሚሹ ግን መልካም ነገር አይጐድልባቸውም።

11. ልጆቼ ሆይ፣ ኑ፤ ስሙኝ፤ እግዚአብሔርን መፍራት አስተምራችኋለሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 34