ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 34:16-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. መታሰቢያቸውን ከምድር ለማጥፋት፣ የእግዚአብሔር ፊት በክፉ አድራጊዎች ላይ ነው።

17. ጻድቃን ሲጮኹ፣ እግዚአብሔር ይሰማቸዋል፤ከመከራቸውም ሁሉ ያድናቸዋል።

18. እግዚአብሔር ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው፤መንፈሳቸው የተሰበረውንም ያድናቸዋል።

19. የጻድቅ መከራው ብዙ ነው፤ እግዚአብሔር ግን ከሁሉም ያድነዋል።

20. ዐጥንቶቹን ሁሉ ይጠብቃል፤ከእነርሱም አንድ አይሰበርም።

21. ኀጢአተኞችን ክፋት ይገድላቸዋል፤ጻድቃንን የሚጠሉ ይፈረድባቸዋል።

22. እግዚአብሔር የባሪያዎቹን ነፍስ ይቤዣል፤እርሱንም መጠጊያ ያደረገ አይፈረድበትም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 34