ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 38:1-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ በቍጣህ አትገሥጸኝ፤በመዓትህም አትቅጣኝ።

2. ፍላጻዎችህ ወግተውኛልና፤እጅህም ተጭናኛለች።

3. ከቍጣህ የተነሣ ሰውነቴ ጤና አጥቶአል፤ከኀጢአቴም የተነሣ ዐጥንቶቼ ሰላም የላቸውም።

4. በደሌ ውጦኛል፤እንደ ከባድ ሸክምም ተጭኖኛል።

5. ከንዝህላልነቴ የተነሣ፣ቍስሌ ሸተተ፤ መገለም፤

6. ዐንገቴን ደፋሁ፤ ጐበጥሁም፤ቀኑንም ሙሉ በትካዜ ተመላለስሁ።

7. ወገቤ እንደ እሳት ነዶአል፤ሰውነቴም ጤና የለውም።

8. እጅግ ዝያለሁ፤ ፈጽሞም ደቅቄአለሁ፤ከልቤም መታወክ የተነሣ እጮኻለሁ።

9. ጌታ ሆይ፤ ምኞቴ ሁሉ በፊትህ ግልጽ ነው፤ጭንቀቴም ከአንተ የተሰወረ አይደለም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 38