ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 46:7-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. የሰራዊት አምላክ ከእኛ ጋር ነው፤የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው። ሴላ

8. ኑና የእግዚአብሔርን ሥራ፣ምድርንም እንዴት ባድማ እንዳደረጋት እዩ።

9. ከዳር እስከ ዳር ጦርነትን ከምድር ያስወግዳል፤ቀስትን ይሰብራል፤ ጦርን ያነክታል፤ጋሻንም በእሳት ያቃጥላል።

10. “ዕረፉ፤ እኔም አምላክ እንደሆንሁ ዕወቁ፤በሕዝቦች ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፤በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።”

11. የሰራዊት አምላክ ከእኛ ጋር ነው፤የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው። ሴላ

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 46