ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 48:7-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. የምሥራቅ ነፋስ የተርሴስን መርከብ እንደሚሰባብር፣አንተ አብረከረክሃቸው።

8. እንደ ሰማን፣በሰራዊት አምላክ ከተማ፣በአምላካችን ከተማ፣እንዲሁ አየን፤እግዚአብሔር ለዘላለም ያጸናታል። ሴላ

9. አምላክ ሆይ፤ በቤተ መቅደስህ ውስጥ ሆነን፣ምሕረትህን እናስባለን።

10. አምላክ ሆይ፤ ምስጋናህ እንደ ስምህ፣እስከ ምድር ዳርቻ ይዘልቃል፤ቀኝ እጅህም ጽድቅን የተሞላች ናት።

11. ስለ ፍርድህ፣የጽዮን ተራራ ሐሤት ታድርግ፤የይሁዳ መንደሮችም ደስ ይበላቸው።

12. በጽዮን አካባቢ ተመላለሱ፤ ዙሪያዋንም ሂዱ፤የጥበቃ ግንበኞቿንም ቍጠሩ፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 48