ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 48:9-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. አምላክ ሆይ፤ በቤተ መቅደስህ ውስጥ ሆነን፣ምሕረትህን እናስባለን።

10. አምላክ ሆይ፤ ምስጋናህ እንደ ስምህ፣እስከ ምድር ዳርቻ ይዘልቃል፤ቀኝ እጅህም ጽድቅን የተሞላች ናት።

11. ስለ ፍርድህ፣የጽዮን ተራራ ሐሤት ታድርግ፤የይሁዳ መንደሮችም ደስ ይበላቸው።

12. በጽዮን አካባቢ ተመላለሱ፤ ዙሪያዋንም ሂዱ፤የጥበቃ ግንበኞቿንም ቍጠሩ፤

13. ለሚቀጥለው ትውልድ ትናገሩ ዘንድ፣መከላከያ ዕርዶቿን ልብ ብላችሁ ተመልከቱ፤መጠበቂያ ማማዎቿን እዩ።

14. ይህ አምላክ ከዘላለም እስከ ዘላለም አምላካችን ነውና፤እስከ መጨረሻው የሚመራንም እርሱ ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 48