ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 5:1-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ ቃሌን አድምጥ፤መቃተቴንም ቸል አትበል።

2. ንጉሤና አምላኬ ሆይ፤ወደ አንተ እጸልያለሁና፣ድረስልኝ ብዬ ስጮህ ስማኝ።

3. እግዚአብሔር ሆይ፤ በማለዳ ድምፄን ትሰማለህ፤በማለዳ ልመናዬን በፊትህ አቀርባለሁ፤ፈቃድህንም በጥሞና እጠባበቃለሁ፤

4. አንተ በክፋት ደስ የምትሰኝ አምላክ አይደለህም፤ክፉም ከአንተ ጋር አያድርም።

5. እብሪተኞች በፊትህ መቆም አይችሉም፤ክፉ አድራጊዎችንም ሁሉ ጠላህ።

6. ሐሰት የሚናገሩትን ታጠፋቸዋለህ፤ደም የተጠሙትንና አታላዮችን፣ እግዚአብሔር ይጸየፋቸዋል።

7. እኔ ግን በምሕረትህ ብዛትወደ ቤትህ እገባለሁ፤አንተንም በመፍራት፣ወደ ተቀደሰው መቅደስህ እሰግዳለሁ።

8. እግዚአብሔር ሆይ፤ ከጠላቶቼ የተነሣ፣በጽድቅህ ምራኝ፤መንገድህንም በፊቴ አቅናልኝ።

9. በንግግራቸው ውስጥ እውነት የለም፤ልባቸው የጥፋት ጐሬ ነው፤ጒሮሮአቸው የተከፈተ መቃብር ነው፤በምላሳቸውም ይሸነግላሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 5