ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 5:4-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. አንተ በክፋት ደስ የምትሰኝ አምላክ አይደለህም፤ክፉም ከአንተ ጋር አያድርም።

5. እብሪተኞች በፊትህ መቆም አይችሉም፤ክፉ አድራጊዎችንም ሁሉ ጠላህ።

6. ሐሰት የሚናገሩትን ታጠፋቸዋለህ፤ደም የተጠሙትንና አታላዮችን፣ እግዚአብሔር ይጸየፋቸዋል።

7. እኔ ግን በምሕረትህ ብዛትወደ ቤትህ እገባለሁ፤አንተንም በመፍራት፣ወደ ተቀደሰው መቅደስህ እሰግዳለሁ።

8. እግዚአብሔር ሆይ፤ ከጠላቶቼ የተነሣ፣በጽድቅህ ምራኝ፤መንገድህንም በፊቴ አቅናልኝ።

9. በንግግራቸው ውስጥ እውነት የለም፤ልባቸው የጥፋት ጐሬ ነው፤ጒሮሮአቸው የተከፈተ መቃብር ነው፤በምላሳቸውም ይሸነግላሉ።

10. አምላክ ሆይ፤ የእጃቸውን ስጣቸው!ተንኰላቸው መውደቂያቸው ይሁን፤ከኀጢአታቸው ብዛት የተነሣ አስወግዳቸው፣በአንተ ላይ ዐምፀዋልና።

11. አንተን መጠጊያ የሚያደርጉ ሁሉ ግን ደስ ይበላቸው፤ዘላለም በደስታ ይዘምሩ፤ስምህን የሚወዱ በአንተ ደስ እንዲላቸው፣ተከላካይ ሁንላቸው።

12. እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ጻድቃንን ትባርካቸዋለህ፤በሞገስህም እንደ ጋሻ ትከልላቸዋለህ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 5