ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 5:8-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. እግዚአብሔር ሆይ፤ ከጠላቶቼ የተነሣ፣በጽድቅህ ምራኝ፤መንገድህንም በፊቴ አቅናልኝ።

9. በንግግራቸው ውስጥ እውነት የለም፤ልባቸው የጥፋት ጐሬ ነው፤ጒሮሮአቸው የተከፈተ መቃብር ነው፤በምላሳቸውም ይሸነግላሉ።

10. አምላክ ሆይ፤ የእጃቸውን ስጣቸው!ተንኰላቸው መውደቂያቸው ይሁን፤ከኀጢአታቸው ብዛት የተነሣ አስወግዳቸው፣በአንተ ላይ ዐምፀዋልና።

11. አንተን መጠጊያ የሚያደርጉ ሁሉ ግን ደስ ይበላቸው፤ዘላለም በደስታ ይዘምሩ፤ስምህን የሚወዱ በአንተ ደስ እንዲላቸው፣ተከላካይ ሁንላቸው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 5