ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 56:4-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. ቃሉን በማመሰግነው አምላክ፣በእግዚአብሔር ታምኛለሁ፤ አልፈራም፤ሥጋ ለባሽ ምን ሊያደርገኝ ይችላል?

5. ቀኑን ሙሉ ቃሌን ያጣምሙታል፤ዘወትርም ሊጐዱኝ ያሤራሉ።

6. ይዶልታሉ፤ ያደባሉ፤ርምጃዬን ይከታተላሉ፤ነፍሴንም ለማጥፋት ይሻሉ።

7. እግዚአብሔር ሆይ፤ ከቶ እንዳያመልጡ፣ሕዝቦቹን በቍጣህ ጣላቸው።

8. ሰቆቃዬን መዝግብ፤እንባዬን በዕቃህ አጠራቅም፤ሁሉስ በመዝገብህ የተያዘ አይደለምን?

9. ወደ አንተ በተጣራሁ ቀን፣ጠላቶቼ ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ፤በዚህም፣ አምላክ ከጐኔ መቆሙን ዐውቃለሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 56