ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 59:2-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. ከክፉ አድራጊዎች ታደገኝ፤ደም ከተጠሙ ሰዎችም አድነኝ።

3. እነሆ በነፍሴ ላይ አድብተዋልና፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ጨካኞች ያለ በደሌ፣ ያለ ኀጢአቴበላዬ ተሰብስበው ዶለቱብኝ።

4. እነርሱ ያለ በደሌ ሊያጠቁኝ ተዘጋጅተው መጡ፤አንተ ግን ትረዳኝ ዘንድ ተነሥ፤ ሁኔታዬንም ተመልከት።

5. የሰራዊት አምላክ የሆንህ፣ አንተ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ሕዝቦችን ሁሉ ለመቅጣት ተነሥ፤በተንኰላቸው በደል የሚፈጽሙትንም ሁሉ አትማራቸው። ሴላ

6. እንደ ውሻ እያላዘኑ፣በምሽት ተመልሰው ይመጣሉ፤በከተማዪቱም ዙሪያ ይራወጣሉ።

7. ከአፋቸው የሚወጣውን ተመልከት፤ሰይፍ በከንፈራቸው ላይ አለ፤“ማን ሊሰማን ይችላል?” ይላሉና።

8. እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ትሥቅባቸዋለህ፤ሕዝቦችን ሁሉ በንቀት ታያቸዋለህ።

9. ብርታቴ ሆይ፤ አንተን እጠብቃለሁ፤አምላክ ሆይ፤ አንተ መጠጊያዬ ነህና።

10. እግዚአብሔር በምሕረቱ ይገናኘኛል፤አምላኬ የጠላቶቼን ውድቀት ያሳየኛል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 59