ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 60:7-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. ገለዓድ የእኔ ነው፤ ምናሴም የእኔ ነው፤ኤፍሬም የራስ ቍሬ ነው፤ይሁዳም በትረ መንግሥቴ ነው።

8. ሞዓብ የመታጠቢያ ገንዳዬ ነው፤በኤዶምያስ ላይ ጫማዬን እወረውራለሁ፤በፍልስጥኤም ላይ በድል እልል እላለሁ።”

9. ወደ ተመሸገው ከተማ ማን ያመጣኛል?ማንስ ወደ ኤዶምያስ ይመራኛል?

10. አምላክ ሆይ፤ የጣልኸን አንተ አይደለህምን?እግዚአብሔር ሆይ፤ ከሰራዊታችን ጋር እኮ አልወጣ አልህ!

11. በጠላት ላይ ድልን አቀዳጀን፤የሰው ርዳታ ከንቱ ነውና።

12. በእግዚአብሔር ክንደ ብርቱ እንሆናለን፤ጠላቶቻችንን የሚረጋግጥልን እርሱ ነውና።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 60