ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 63:1-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ አምላኬ ነህ፤አንተን ከልብ እሻለሁ፤ ውሃ በሌለበት፣በደረቅና በተራቈተ ምድር፣ነፍሴ አንተን ተጠማች፤ሥጋዬም አንተን ናፈቀች።

2. ስለዚህ በመቅደስ ውስጥ አየሁህ፤ኀይልህንና ክብርህንም ተመለከትሁ።

3. ምሕረትህ ከሕይወት ይበልጣልና፤ከንፈሮቼ ያመሰግኑሃል።

4. እንግዲህ፣ በሕይወቴ ዘመን አመሰግንሃለሁ፤በአንተም ስም እጆቼን አነሣለሁ።

5. ነፍሴ በቅቤና በሥብ እንደሚረካ ሰው ትረካለች፤አፌም በሚያዜሙ ከንፈሮች በደስታ ያወድስሃል።

6. በመኝታዬ አስብሃለሁ፤ሌሊቱንም ሁሉ ስለ አንተ አሰላስላለሁ።

7. አንተ ረዳቴ ነህና፣በክንፎችህ ሥር ተጠልዬ በደስታ እዘምራለሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 63