ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 63:2-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. ስለዚህ በመቅደስ ውስጥ አየሁህ፤ኀይልህንና ክብርህንም ተመለከትሁ።

3. ምሕረትህ ከሕይወት ይበልጣልና፤ከንፈሮቼ ያመሰግኑሃል።

4. እንግዲህ፣ በሕይወቴ ዘመን አመሰግንሃለሁ፤በአንተም ስም እጆቼን አነሣለሁ።

5. ነፍሴ በቅቤና በሥብ እንደሚረካ ሰው ትረካለች፤አፌም በሚያዜሙ ከንፈሮች በደስታ ያወድስሃል።

6. በመኝታዬ አስብሃለሁ፤ሌሊቱንም ሁሉ ስለ አንተ አሰላስላለሁ።

7. አንተ ረዳቴ ነህና፣በክንፎችህ ሥር ተጠልዬ በደስታ እዘምራለሁ።

8. ነፍሴ አንተን የሙጥኝ ብላለች፤ቀኝ እጅህም ደግፋ ይዛኛለች።

9. ነፍሴን ለማጥፋት የሚሹ ግን፣ወደ ምድር ጥልቅ ይወርዳሉ፤

10. ለሰይፍ አልፈው ይሰጣሉ፤የቀበሮዎችም ምግብ ይሆናሉ።

11. ንጉሥ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለዋል፤በእግዚአብሔርም ስም ቃል የሚገቡ ሁሉ ይከብራሉ፤የሐሰተኞች አንደበትም ትዘጋለች።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 63