ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 63:7-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. አንተ ረዳቴ ነህና፣በክንፎችህ ሥር ተጠልዬ በደስታ እዘምራለሁ።

8. ነፍሴ አንተን የሙጥኝ ብላለች፤ቀኝ እጅህም ደግፋ ይዛኛለች።

9. ነፍሴን ለማጥፋት የሚሹ ግን፣ወደ ምድር ጥልቅ ይወርዳሉ፤

10. ለሰይፍ አልፈው ይሰጣሉ፤የቀበሮዎችም ምግብ ይሆናሉ።

11. ንጉሥ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለዋል፤በእግዚአብሔርም ስም ቃል የሚገቡ ሁሉ ይከብራሉ፤የሐሰተኞች አንደበትም ትዘጋለች።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 63