ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 66:1-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል ይበል!

2. ለስሙ ክብር ዘምሩ፤ውዳሴውንም አድምቁ

3. እግዚአብሔርን እንዲህ በሉት፤ “ሥራህ እንዴት ግሩም ነው!ጠላቶችህ ከኀይልህ ታላቅነት የተነሣ፣በፊትህ ይርዳሉ።

4. ምድር ሁሉ ይሰግድልሃል፤በዝማሬ ያመሰግኑሃል፤ለስምህም ይዘምራሉ። ሴላ

5. ኑና፣ እግዚአብሔር ያደረገውን እዩበሰዎች መካከል ሥራው አስፈሪ ነው!

6. ባሕሩን የብስ አደረገው፤ወንዙን በእግር ተሻገሩ፤ኑ፣ በእርሱ ደስ ይበለን።

7. በኀይሉ ለዘላለም ይገዛል፤ዐይኖቹ ሕዝቦችን ይመለከታሉ፤እንግዲህ ዐመፀኞች ቀና ቀና አይበሉ። ሴላ

8. ሕዝቦች ሆይ፤ አምላካችንን ባርኩ፤የምስጋናውንም ድምፅ አሰሙ።

9. እኛን በሕይወት የሚያኖረን፣እግራችንንም ከመንሸራተት የሚጠብቅ እርሱ ነው።

10. አምላክ ሆይ፤ አንተ ፈተንኸን፤እንደ ብርም አነጠርኸን።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 66