ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 66:11-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. ወደ ወጥመድ አገባኸን፤በጀርባችንም ሸክም ጫንህብን።

12. ሰዎች በራሳችን ላይ እንዲፈነጩ አደረግህ፤በእሳትና በውሃ መካከል አለፍን፤የኋላ ኋላ ግን ወደ በረከት አመጣኸን።

13. የሚቃጠል መሥዋዕት ይዤ ወደ መቅደስህ እገባለሁ፤ስእለቴንም ለአንተ እፈጽማለሁ፤

14. በመከራ ጊዜ ከአፌ የወጣ፣በከንፈሬም የተናገርሁት ስእለት ነው።

15. ፍሪዳዎችን የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጌ፣አውራ በጎችንም የሚጤስ ቍርባን አድርጌ አቀርብልሃለሁ፤ኰርማዎችንና ፍየሎችንም እሠዋልሃለሁ። ሴላ

16. እግዚአብሔርን የምትፈሩ ሁሉ፤ ኑና ስሙ፤ለነፍሴ ያደረገላትን ልንገራችሁ።

17. በአፌ ወደ እርሱ ጮኽሁ፤በአንደበቴም አመሰገንሁት።

18. ኀጢአትን በልቤ አስተናግጄ ቢሆን ኖሮ፣ጌታ ባልሰማኝ ነበር።

19. አሁን ግን እግዚአብሔር በእርግጥ ሰምቶኛል፤ጸሎቴንም አድምጦአል።

20. ጸሎቴን ያልናቀ፣ምሕረቱንም ከእኔ ያላራቀ፣እግዚአብሔር ምስጋና ይድረሰው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 66