ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 66:16-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. እግዚአብሔርን የምትፈሩ ሁሉ፤ ኑና ስሙ፤ለነፍሴ ያደረገላትን ልንገራችሁ።

17. በአፌ ወደ እርሱ ጮኽሁ፤በአንደበቴም አመሰገንሁት።

18. ኀጢአትን በልቤ አስተናግጄ ቢሆን ኖሮ፣ጌታ ባልሰማኝ ነበር።

19. አሁን ግን እግዚአብሔር በእርግጥ ሰምቶኛል፤ጸሎቴንም አድምጦአል።

20. ጸሎቴን ያልናቀ፣ምሕረቱንም ከእኔ ያላራቀ፣እግዚአብሔር ምስጋና ይድረሰው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 66