ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 66:5-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. ኑና፣ እግዚአብሔር ያደረገውን እዩበሰዎች መካከል ሥራው አስፈሪ ነው!

6. ባሕሩን የብስ አደረገው፤ወንዙን በእግር ተሻገሩ፤ኑ፣ በእርሱ ደስ ይበለን።

7. በኀይሉ ለዘላለም ይገዛል፤ዐይኖቹ ሕዝቦችን ይመለከታሉ፤እንግዲህ ዐመፀኞች ቀና ቀና አይበሉ። ሴላ

8. ሕዝቦች ሆይ፤ አምላካችንን ባርኩ፤የምስጋናውንም ድምፅ አሰሙ።

9. እኛን በሕይወት የሚያኖረን፣እግራችንንም ከመንሸራተት የሚጠብቅ እርሱ ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 66