ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 70:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. አምላክ ሆይ፤ ታድነኝ ዘንድ ዘንበል በል፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔን ለመርዳት ፍጠን።

2. ሕይወቴን ለማጥፋት የሚሹ፣ይፈሩ፤ ሁከትም ይምጣባቸው፤ የእኔን መጐዳት የሚመኙ፣በውርደት ወደ ኋላቸው ይመለሱ።

3. በእኔ ላይ፣ “እሰይ! እሰይ!” የሚሉ፣ተሸማቀው ወደ ኋላ ይመለሱ።

4. ነገር ግን የሚሹህ ሁሉ፣በአንተ ሐሤት ያድርጉ፤ ደስም ይበላቸው፤“ማዳንህን የሚወዱ ሁሉ ሁል ጊዜ፣እግዚአብሔር ከፍ ይበል!” ይበሉ።

5. እኔ ግን ምስኪንና ችግረኛ ነኝ፤አምላክ ሆይ፤ ፈጥነህ ድረስልኝ፤ረዳቴም፣ ታዳጊዬም አንተ ነህና፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አትዘግይ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 70