ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 72:1-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ ፍትህን ለንጉሥ፣ጽድቅህንም ለንጉሥ ልጅ ዐድል፤

2. እርሱም ሕዝብህን በጽድቅ ይዳኛል፤ለተቸገሩትም በትክክል ይፈርዳል።

3. ተራሮች ብልጽግናን፣ኰረብቶችም የጽድቅን ፍሬ ለሕዝቡ ያመጣሉ።

4. ለተቸገረው ሕዝብ ይሟገታል፤የድኾችን ልጆች ያድናል፤ጨቋኙንም ያደቀዋል።

5. ፀሓይ እስካለች ድረስ፣ጨረቃም በምትኖርበት ዘመን ሁሉ፣ ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል።

6. እንደ ዝናብ በታጨደ መስክ ላይ ይወርዳል፤እንደ ካፊያም ምድርን ያረሰርሳል።

7. በዘመኑ ጽድቅ ይሰፍናል፤ጨረቃ ከስፍራዋ እስከምትታጣ ድረስም ሰላም ይበዛል።

8. ከባሕር እስከ ባሕር ድረስ፣ከታላቁም ወንዝ እስከ ምድር ዳርቻ ይገዛል።

9. የበረሓ ዘላኖች በፊቱ ይሰግዳሉ፤ጠላቶቹም ዐፈር ይልሳሉ።

10. የተርሴስና የደሴቶች ነገሥታት፣ግብር ያመጡለታል፤የዐረብና የሳባ ነገሥታት፣እጅ መንሻ ያቀርባሉ።

11. ነገሥታት ሁሉ ይሰግዱለታል፤ሕዝቦችም ሁሉ ይገዙለታል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 72