ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 72:8-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. ከባሕር እስከ ባሕር ድረስ፣ከታላቁም ወንዝ እስከ ምድር ዳርቻ ይገዛል።

9. የበረሓ ዘላኖች በፊቱ ይሰግዳሉ፤ጠላቶቹም ዐፈር ይልሳሉ።

10. የተርሴስና የደሴቶች ነገሥታት፣ግብር ያመጡለታል፤የዐረብና የሳባ ነገሥታት፣እጅ መንሻ ያቀርባሉ።

11. ነገሥታት ሁሉ ይሰግዱለታል፤ሕዝቦችም ሁሉ ይገዙለታል።

12. ችግረኛው በጮኸ ጊዜ፣ምስኪኑንና ረዳት የሌለውን ይታደገዋል።

13. ለድኾችና ለችግረኞች ይራራል፤ምስኪኖችንም ከሞት ያድናል።

14. ሕይወታቸውን ከጭቈናና ከግፍ ያድናል፤ደማቸውም በእርሱ ፊት ክቡር ነው።

15. ዕድሜው ይርዘም!ከዐረብ ወርቅ ይምጣለት፤ዘወትር ይጸልዩለት፤ቀኑንም ሙሉ ይባርኩት።

16. በምድሪቱ ላይ እህል ይትረፍረፍ፤በተራሮችም ዐናት ላይ ይወዛወዝ።ፍሬው እንደ ሊባኖስ ይንዠርገግ፤በከተማ ያለውም እንደ ሜዳ ሣር እጅብ ብሎ ይውጣ።

17. ስሙ ለዘላለም ጸንቶ ይኑር፤ዝናው ፀሓይ የምትኖረውን ዘመን ያህል ይዝለቅ፤ሕዝቦች ሁሉ በእርሱ ይባረኩ፤ሕዝቡ ሁሉ ቡሩክ ነህ ይበለው።

18. ብቻውን ድንቅ ነገር የሚያደርግ፣የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ።

19. ክቡር ስሙ ለዘላለም ይባረክ፤ምድርም ሁሉ በክብሩ ይሞላ።አሜን፤ አሜን።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 72