ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 73:10-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. ስለዚህ ሕዝቡ ወደ እነርሱ ይነጒዳል፤ውሃቸውንም በገፍ ይጠጣሉ።

11. “ለመሆኑ እግዚአብሔር እንዴት ያውቃል?በልዑልስ ዘንድ ዕውቀት አለ?” ይላሉ።

12. እንግዲህ፣ ክፉዎች ይህን ይመስላሉ፤ሁል ጊዜ ግድ የለሽና ሀብት በሀብት ናቸው።

13. ለካ ልቤን ንጹሕ ያደረግሁት በከንቱ ነው፤እጄንም በየዋህነት የታጠብሁት በከንቱ ኖሮአል!

14. ቀኑን ሙሉ ተቀሠፍሁ፤ጠዋት ጠዋትም ተቀጣሁ።

15. “እኔ እንደዚህ እናገራለሁ” ብልማ ኖሮ፣የልጆችህን ትውልድ በከዳሁ ነበር።

16. ይህን ነገር ለመረዳት በሞከርሁ ጊዜ፣አድካሚ ተግባር መስሎ ታየኝ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 73