ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 73:24-28 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

24. በምክርህ መራኸኝ፤ኋላም ወደ ክብር ታስገባኛለህ።

25. በሰማይ ከአንተ በቀር ማን አለኝ?በምድርም ከአንተ ሌላ የምሻው የለኝም።

26. ሥጋዬና ልቤ ሊደክሙ ይችላሉ፤እግዚአብሔር ግን የልቤ ብርታት፣የዘላለም ዕድል ፈንታዬ ነው።

27. እነሆ፤ ከአንተ የሚርቁ ይጠፋሉና፤አንተ ታማኞች ያልሆኑልህን ሁሉ ታጠፋቸዋለህ።

28. ለእኔ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል፤ጌታ እግዚአብሔርን መጠጊያዬ አድርጌዋለሁ፤ስለ ሥራህም ሁሉ እናገር ዘንድ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 73