ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 73:3-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. ክፉዎች ሲሳካላቸው አይቼ፣በዐመፀኞች ቀንቼ ነበርና።

4. አንዳች ጣር የለባቸውም፤ሰውነታቸውም ጤናማና የተደላደለ ነው።

5. በሰዎች የሚደርሰው ጣጣ አይደርስባቸውም፤እንደ ማንኛውም ሰው መከራ አያገኛቸውም።

6. ስለዚህ ትዕቢት የዐንገት ጌጣቸው ነው፤ዐመፅንም እንደ ልብስ ተጐናጽፈዋል።

7. የሰባ ዐይናቸው ይጒረጠረጣል፤ልባቸውም በከንቱ ሐሳብ ተሞልቶ ይፈስሳል።

8. በፌዝና በክፋት ይናገራሉ፤ቀና ቀና ብለውም በዐመፅ ይዝታሉ።

9. አፋቸውን በሰማይ ላይ ያላቅቃሉ፤አንደበታቸውም ምድርን ያካልላል።

10. ስለዚህ ሕዝቡ ወደ እነርሱ ይነጒዳል፤ውሃቸውንም በገፍ ይጠጣሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 73