ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 73:5-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. በሰዎች የሚደርሰው ጣጣ አይደርስባቸውም፤እንደ ማንኛውም ሰው መከራ አያገኛቸውም።

6. ስለዚህ ትዕቢት የዐንገት ጌጣቸው ነው፤ዐመፅንም እንደ ልብስ ተጐናጽፈዋል።

7. የሰባ ዐይናቸው ይጒረጠረጣል፤ልባቸውም በከንቱ ሐሳብ ተሞልቶ ይፈስሳል።

8. በፌዝና በክፋት ይናገራሉ፤ቀና ቀና ብለውም በዐመፅ ይዝታሉ።

9. አፋቸውን በሰማይ ላይ ያላቅቃሉ፤አንደበታቸውም ምድርን ያካልላል።

10. ስለዚህ ሕዝቡ ወደ እነርሱ ይነጒዳል፤ውሃቸውንም በገፍ ይጠጣሉ።

11. “ለመሆኑ እግዚአብሔር እንዴት ያውቃል?በልዑልስ ዘንድ ዕውቀት አለ?” ይላሉ።

12. እንግዲህ፣ ክፉዎች ይህን ይመስላሉ፤ሁል ጊዜ ግድ የለሽና ሀብት በሀብት ናቸው።

13. ለካ ልቤን ንጹሕ ያደረግሁት በከንቱ ነው፤እጄንም በየዋህነት የታጠብሁት በከንቱ ኖሮአል!

14. ቀኑን ሙሉ ተቀሠፍሁ፤ጠዋት ጠዋትም ተቀጣሁ።

15. “እኔ እንደዚህ እናገራለሁ” ብልማ ኖሮ፣የልጆችህን ትውልድ በከዳሁ ነበር።

16. ይህን ነገር ለመረዳት በሞከርሁ ጊዜ፣አድካሚ ተግባር መስሎ ታየኝ።

17. ይኸውም ወደ አምላክ መቅደስ እስክገባ፣መጨረሻቸውንም እስካይ ድረስ ነበር።

18. በእርግጥ በሚያዳልጥ ስፍራ አስቀመጥኻቸው፤ወደ ጥፋትም አወረድሃቸው።

19. እንዴት ፈጥነው በቅጽበት ጠፉ!በድንጋጤ ፈጽመው ወደሙ።

20. ሰው ከሕልሙ ሲነቃ እንደሚሆነው፣ጌታ ሆይ፤ አንተም በምትነሣበት ጊዜ፣እንደ ቅዠት ከንቱ ታደርጋቸዋለህ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 73