ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 75:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. አምላክ ሆይ፤ ምስጋና እናቀርብልሃለን፤ስምህ ቅርብ ነውና ምስጋና እናቀርብልሃለን፤ሰዎችም ስለ ድንቅ ሥራህ ይናገራሉ።

2. አንተም እንዲህ አልህ፤ “ለይቼ በወሰንኋት ሰዓት፣በቅን የምፈርድ እኔ ነኝ።

3. ምድርና ሕዝቦቿ ሁሉ በሚናወጡበት ጊዜ፣ምሰሶቿን አጽንቼ የምይዝ እኔ ነኝ። ሴላ

4. እብሪተኛውን፣ ‘አትደንፋ’፤ክፉውንም ‘ቀንድህን ከፍ አታድርግ እለዋለሁ፤

5. ቀንድህን ወደ ሰማይ አታንሣ፤ዐንገትህንም መዝዘህ አትናገር።’ ”

6. ክብር ከምሥራቅ ወይም ከምዕራብ፣ወይም ከምድረ በዳ አይመጣምና፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 75