ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 75:6-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. ክብር ከምሥራቅ ወይም ከምዕራብ፣ወይም ከምድረ በዳ አይመጣምና፤

7. ነገር ግን የሚፈርድ እግዚአብሔር ነው፤እርሱ አንዱን ዝቅ፣ ሌላውን ከፍ ያደርጋል።

8. በእግዚአብሔር እጅ ጽዋ አለ፤በሚገባ የተቀመመና ዐረፋ የሚወጣው የወይን ጠጅ ሞልቶበታል፤ይህን ከውስጡ ወደ ውጭ ገለበጠው፤የምድር ዐመፀኞችም አተላው ሳይቀር ይጨልጡታል።

9. እኔ ግን ይህን ለዘላለም ዐውጃለሁ፤ለያዕቆብም አምላክ ዝማሬ አቀርባለሁ።

10. የክፉዎችን ሁሉ ቀንድ እሰብራለሁ፤የጻድቃን ቀንድ ግን ከፍ ከፍ ይላል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 75