ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 77:9-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. እግዚአብሔር ቸርነቱን ዘነጋ?ወይስ ከቍጣው የተነሣ ርኅራኄውን ነፈገ?።” ሴላ

10. እኔም፣ “የልዑል ቀኝ እጅ እንደ ተለወጠ ማሰቤ፣ይህ ድካሜ ነው” አልሁ።

11. የእግዚአብሔርን ሥራ አስታውሳለሁ፤የጥንት ታምራትህን በእርግጥ አስታውሳለሁ፤

12. ሥራህን ሁሉ አሰላስላለሁ፤ድንቅ ሥራህን ሁሉ አውጠነጥናለሁ።

13. አምላክ ሆይ፤ መንገድህ ቅዱስ ነው፤እንደ አምላካችን ያለ ታላቅ አምላክ ማን ነው?

14. ታምራትን የምታደርግ አምላክ አንተ ነህ፤በሕዝቦችም መካከል ኀይልህን ትገልጣለህ።

15. የያዕቆብንና የዮሴፍን ልጆች፣ሕዝብህን በክንድህ ተቤዠሃቸው። ሴላ

16. አምላክ ሆይ፤ ውሆች አዩህ፤ውሆች አንተን አይተው ተሸማቀቁ፤ጥልቆችም ተነዋወጡ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 77