ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 78:5-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. ለያዕቆብ ሥርዐትን መሠረተ፤በእስራኤልም ሕግን ደነገገ፤ልጆቻቸውንም እንዲያስተምሩ፣አባቶቻችንን አዘዘ።

6. ይህም የሚቀጥለው ትውልድ እንዲያውቅ፣እነርሱም በተራቸው ለልጆቻቸው፣ገና ለሚወለዱት እንዲነግሩ ነው።

7. እነርሱም በእግዚአብሔር ይታመናሉ፤ የእግዚአብሔርን ሥራ አይረሱም፤ትእዛዞቹንም ይጠብቃሉ።

8. ነገር ግን እንደ አባቶቻቸው፣እልከኞችና ዐመፀኞች፣ልቡን ያላቀና፣መንፈሱም በእግዚአብሔር የማይታመን ትውልድ አይሆኑም።

9. የኤፍሬም ልጆች የታጠቁ ቀስተኞች ቢሆኑም፣በጦርነት ቀን ወደ ኋላ ተመለሱ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 78