ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 79:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. አምላክ ሆይ፤ ሕዝቦች ርስትህን ወረሩ፤የተቀደሰውን ቤተ መቅደስህን አረከሱ፤ኢየሩሳሌምንም አፈራርሰው ጣሏት።

2. የባሪያዎችህን ሬሳ ለሰማይ ወፎች፣የቅዱሳንህንም ሥጋ ለምድር አራዊት፣ምግብ አድርገው ሰጡ።

3. ደማቸውንም በኢየሩሳሌም ዙሪያ፣እንደ ውሃ አፈሰሱ፤የሚቀብራቸውም አልተገኘም።

4. እኛም ለጎረቤቶቻችን መዘባበቻ፣በዙሪያችንም ላሉት መሣቂያ መሣለቂያ ሆንን።

5. እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህ እስከ መቼ ነው?የምትቈጣውስ ለዘላለም ነውን?ቅናትህስ እንደ እሳት ሲነድ ይኖራልን?

6. በማያውቁህ ሕዝቦች ላይ፣ስምህን በማይጠሩ፣መንግሥታት ላይ፣መዓትህን አፍስስ፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 79