ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 81:1-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ብርታታችን ለሆነው አምላክ በደስታ ዘምሩ፤ለያዕቆብ አምላክ እልል በሉ።

2. ዝማሬውን ጀምሩ፤ ከበሮውን ምቱ፤በበገናና በመሰንቆ ጥዑም ዜማ አሰሙ።

3. በሙሉ ጨረቃ፣ በክብረ በዓላችን ዕለት፣በወሩ መግቢያ፣ ጨረቃ ስትወለድ መለከት ንፉ፤

4. ይህ ለእስራኤል የተሰጠ ሥርዐት፣የያዕቆብም አምላክ ድንጋጌ ነውና።

5. ሙሉ ለሙሉ ግብፅን ለቆ በወጣ ጊዜ፣ይህን ለዮሴፍ ደነገገለት፤በማላውቀውም ቋንቋ እንዲህ ሲል ሰማሁ፦

6. “ትከሻውን ከሸክም ገላገልሁት፤እጁንም ቅርጫት ከመያዝ አሳረፍሁ።

7. በመከራህ ጊዜ ጠራኸኝ፤ እኔም ታደግሁህ፤በነጐድጓድ መሰወሪያ ውስጥ መለስሁልህ፤በመሪባ ውሃ ዘንድ ፈተንሁህ። ሴላ

8. “ሕዝቤ ሆይ፤ ሳስጠነቅቅህ ስማኝ፤እስራኤል ሆይ፤ ምነው ብታደምጠኝ!

9. በአንተ ዘንድ ባዕድ አምላክ አይኑር፤ለሌላም አምላክ አትስገድ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 81