ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 83:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. አምላክ ሆይ፤ ዝም አትበል፤አምላክ ሆይ፤ ጸጥ አትበል፤ ጭጭ አትበል።

2. ጠላቶችህ እንዴት እንደ ተነሣሡ፣ባላንጣዎችህም እንዴት ራሳቸውን ቀና ቀና እንዳደረጉ ተመልከት።

3. በሕዝብህ ላይ በተንኰል አሤሩ፤በውድ ልጆችህ ላይ በአንድነት ተመካከሩ።

4. “የእስራኤል ስም ከእንግዲህ እንዳይታወስ፣ኑና ሕዝብ እንዳይሆኑ እንደምስሳቸው” አሉ።

5. በአንድ ሐሳብ ተስማምተው ተማከሩ፤በአንተም ላይ ተማማሉ፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 83