ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 83:9-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. በምድያም ላይ እንዳደረግኸው አድርግባቸው፤በቂሶንም ወንዝ በሲሣራና በኢያቢስ ላይ ያደረስኸው ይድረስባቸው።

10. እነርሱም በዐይንዶር ጠፉ፤እንደ ምድርም ጒድፍ ሆኑ።

11. መኳንንታቸውን እንደ ሔሬብና እንደ ዜብ፣መሳፍንታቸውንም ሁሉ እንደ ዛብሄልና እንደ ስልማና አድርጋቸው፤

12. እነዚህም፣ “የእግዚአብሔርን የግጦሽ ቦታ፣ወስደን የግላችን እናድርግ” የሚሉ ናቸው።

13. አምላኬ ሆይ፤ በዐውሎ ነፋስ እንደሚነዳ ትቢያ፣በነፋስም ፊት እንዳለ ገለባ አድርጋቸው።

14. እሳት ደንን እንደሚያጋይ፣ነበልባልም ተራራን እንደሚያቃጥል፣

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 83