ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 89:45-52 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

45. የወጣትነት ዘመኑን አሳጠርኸው፤ዕፍረትንም አከናነብኸው። ሴላ

46. እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህ እስከ መቼ ይሆናል? ራስህንስ ለዘላለም ትሰውራለህን?ቍጣህስ እንደ እሳት የሚነደው እስከ መቼ ነው?

47. ዘመኔ ምን ያህል አጭር እንደሆነች አስብ፤የሰውን ልጆች እንዲያው ለከንቱ ፈጠርሃቸው!

48. ሞትን ሳያይ ሕያው ሆኖ የሚቀርሰው አለን?ራሱን ከሲኦል እጅ ማዳን የሚችል ማን ነው? ሴላ

49. ጌታ ሆይ፤ ለዳዊት በታማኝነትህ የማልህለት፣የቀድሞው ምሕረትህ የት አለ?

50. ጌታ ሆይ፤ ባሪያህ እንዴት እንደ ተፌዘበት፣የብዙ ሰዎችንም ነቀፋ እንደ ታቀፍሁ አስብ።

51. እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላቶችህ የተሣለቁበትን፣የቀባኸውን ሰው እርምጃ የነቀፉበትን ሁኔታ አስብ።

52. እግዚአብሔር ለዘላለም ይባረክ፤አሜን፤ አሜን።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 89