ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 89:6-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. በላይ በሰማያት ከእግዚአብሔር ጋር ማን ሊስተካከል ይችላል?ከሰማያውያን ፍጥረታትስ መካከል ማን እግዚአብሔርን ይመስለዋል?

7. እግዚአብሔር በቅዱሳን ጉባኤ መካከል በጣም የሚፈራ፣በዙሪያውም ካሉት ሁሉ በላይ እጅግ የሚከበር ነው።

8. የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ አንተ ያለ ማን ነው? እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ኀያል ነህ፤ ታማኝነትህም ከብቦሃል።

9. የባሕርን ቍጣ ትቈጣጠራለህ፤ሞገዱም ሲነሣ ጸጥ ታደርገዋለህ።

10. አንተ ረዓብን የተሰየፈ ያህል አደቀቅኸው፤በብርቱ ክንድህም ጠላቶችህን በተንሃቸው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 89