ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 9:14-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. ይህን ስታደርግልኝ፣ በጽዮን ሴት ልጅ ደጅ፣ምስጋናህን ዐውጃለሁ፤በማዳንህም ሐሤት አደርጋለሁ።

15. አሕዛብ በቈፈሩት ጒድጓድ ገቡ፤እግራቸውም ራሳቸው በስውር ባስቀመጡት ወጥመድ ተያዘ።

16. እግዚአብሔር በትክክለኛ ፍርዱ የታወቀ ነው፤ክፉዎችም በእጃቸው ሥራ ተጠመዱ። ሒጋዮን ሴላ

17. ክፉዎች ተመልሰው ወደ ሲኦል ይወርዳሉ፤እግዚአብሔርን የሚዘነጉ ሕዝቦችም ሁሉ እንደዚሁ።

18. ችግረኞች ግን መቼም ቢሆን አይረሱም፤የድኾችም ተስፋ ለዘላለም መና ሆኖ አይቀርም።

19. እግዚአብሔር ሆይ ተነሥ፤ ሰውም አያይል፤አሕዛብም በፊትህ ይፈረድባቸው።

20. እግዚአብሔር ሆይ፤ ድንጋጤ አምጣባቸው፤ሕዝቦች ሰው ከመሆን እንደማያልፉ ይወቁ። ሴላ

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 9