ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 9:6-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. ጠላቶች ለዘላለም ጠፉ፤ከተሞቻቸውንም ገለባበጥሃቸው፤መታሰቢያቸውም ተደምስሶአል።

7. እግዚአብሔር ግን ለዘላለም በዙፋኑ ላይ ነው፤መንበሩንም ለፍርድ አጽንቶአል።

8. ዓለምን በጽድቅ ይዳኛል፤ሕዝቦችንም በፍትሕ ይገዛል።

9. እግዚአብሔር ለተጨቈኑት ዐምባ ነው፤በመከራም ጊዜ መጠጊያ ይሆናቸዋል።

10. ስምህን የሚያውቁ ይታመኑብሃል፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ የሚሹህን አትተዋቸውምና።

11. በጽዮን ለሚኖር ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ሥራውንም በሕዝቦች መካከል በግልጽ አውሩ፤

12. ደም ተበቃዩ ዐስቦአቸዋልና፤የጭቍኖችንም ጩኸት አልዘነጋም።

13. እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላቶቼ የሚያደርሱብኝን መከራ ተመልከት፤አይተህም ራራልኝ፤ ከሞት ደጅም አንሥተህ መልሰኝ፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 9