ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 91:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. በልዑል መጠጊያ የሚኖር፣ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ሥር ያድራል።

2. እግዚአብሔርን፣ “መጠጊያዬ፣ ምሽጌ፣የምታመንብህ አምላኬ” እለዋለሁ።

3. እርሱ ከአዳኝ ወጥመድ፣ከአሰቃቂ ቸነፈር ያድንሃልና።

4. በላባዎቹ ይጋርድሃል፤በክንፎቹ ሥር መሸሸጊያ ታገኛለህ፤ታማኝነቱ ጋሻና መከታ ይሆንሃል።

5. የሌሊትን አስደንጋጭነት፣በቀን የሚወረወረውንም ፍላጻ አትፈራም፤

6. በጨለማ የሚያደባ ቸነፈር፣በቀትር ረፍራፊውም አያሠጋህም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 91