ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 92:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔርን ማመስገን መልካም ነው፤ልዑል ሆይ፤ ለስምህ መዘመር ጥሩ ነው፤

2. ምሕረትህን በማለዳ፣ታማኝነትህንም በሌሊት ማወጅ መልካም ነው፤

3. ዐሥር አውታር ባለው በገና፣በመሰንቆም ቅኝት ታጅቦ ማወጅ ጥሩ ነው።

4. እግዚአብሔር ሆይ፤ በሥራህ ስለ ተደሰትሁ፣ስለ እጅህ ሥራ በደስታ እዘምራለሁ።

5. እግዚአብሔር ሆይ፤ ሥራህ እንዴት ታላቅ ነው!ሐሳብህስ ምን ያህል ጥልቅ ነው!

6. ደነዝ ሰው ይህን አያውቅም፤ነኁላላም አያስተውለውም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 92