ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 92:11-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. ዐይኖቼ የባላንጦቼን ውድቀት አዩ፤ጆሮዎቼም የክፉ ጠላቶቼን ድቀት ሰሙ።

12. ጻድቃን እንደ ዘንባባ ይንሰራፋሉ፤እንደ ሊባኖስ ዝግባም ይንዠረገጋሉ።

13. በእግዚአብሔር ቤት ተተክለዋል፤በአምላካችንም አደባባይ ይንሰራፋሉ።

14. ባረጁ ጊዜ እንኳ ያፈራሉ፤እንደ ለመለሙና እንደ ጠነከሩም ይኖራሉ።

15. “እግዚአብሔር ትክክለኛ ነው፤እርሱ ዐለቴ ነው፤ በእርሱ ዘንድ እንከን የለም” ይላሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 92