ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 94:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. የበቀል አምላክ፣ አንተ እግዚአብሔር ሆይ፤የበቀል አምላክ ሆይ፤ ደምቀህ ተገለጥ።

2. አንተ የምድር ዳኛ ሆይ፤ ተነሥ፤ለትዕቢተኞች የእጃቸውን ስጣቸው።

3. ክፉዎች እስከ መቼ እግዚአብሔር ሆይ፤ ክፉዎች እስከ መቼ ይፈነጫሉ?

4. የእብሪት ቃላት ያዥጐደጒዳሉ፤ክፉ አድራጊዎች ሁሉ ጒራ ይነዛሉ።

5. እግዚአብሔር ሆይ፤ ሕዝብህን አደቀቁ፤ርስትህንም አስጨነቁ።

6. መበለቲቱንና መጻተኛውን ገደሉ፤የድኻ አደጉንም ነፍስ አጠፉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 94